ሞትን ለዘለዓለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ ይህን ጌታ ተናግሮአል።
ሮሜ 8:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንም አይለየንም፤ በዚህ ሁሉ በወደደን በርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ በወደደን በክርስቶስ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ድል በመንሣት ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በወደደን በእርሱ ሁሉን ድል እንነሣለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። |
ሞትን ለዘለዓለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ ይህን ጌታ ተናግሮአል።
በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፤”
ለእናንተ ስለ ራሳችን ሁልጊዜ መልስ የምንሰጥ ይመስላችኋልን? በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን፤ ነገር ግን፥ ወዳጆቼ! እናንተን ለማነጽ ስንል ሁሉን እንናገራለን።
እርሱ ግን፥ “ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ኀይሌ በድካም ፍጹም ይሆናል” አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል እንዲያድርብኝ በበለጠ ደስታ በድካሜ መመካትን እወዳለሁ።
ክርስቶስ በእኔ ይኖራል እንጂ ከእንግዲህ ወዲያ እኔ አልኖርም፤ አሁን በሥጋ የምኖረው በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ በማመን የምኖረው ነው።
ክርስቶስም እንዳፈቀራችሁ፥ ስለ እናንተም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ ያለው መባንና መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፥ በፍቅር ተመላለሱ።
ፍቅር በዚህ ነው፥ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን ነገር ግን እርሱ እንደ ወደደን እና ለኃጢአታችንም ማስተስሪያ እንዲሆን ልጁን ስለላከልን ነው።
እንዲሁም ከታመነው ምስክር፥ ከሙታን በኩር ከሆነው፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ፤ ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉት የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ናቸው።”
እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።