Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዮሐንስ 4:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ፥ አሸንፋችኋቸዋልም፥ በእናንተ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ልጆች ሆይ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ፤ እነርሱንም አሸንፋችኋቸዋል፤ ምክንያቱም በእናንተ ውስጥ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ልጆች ሆይ! እናንተ የእግዚአብሔር ናችሁ፤ በእናንተ ያለው መንፈስ በዓለም ካለው መንፈስ ይበልጣል። ስለዚህ ሐሰተኞች ነቢያትን አሸንፋችኋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።

Ver Capítulo Copiar




1 ዮሐንስ 4:4
28 Referencias Cruzadas  

እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?


ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።


በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።


ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነናልም። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፥ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።


እኛ ግን፥ እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር በነፃ የተሰጠንን፥ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም።


እኛ ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን፥ መላው ዓለምም በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።


በእርሱ እንደምንኖር እሱም በእኛ እንደሚኖር በዚህ እናውቃለን፥ ምክንያቱም ከመንፈሱ ስለ ሰጠን ነው።


በተረፈ በጌታ በኃይሉ ብርታትም ጠንክሩ።


ሥር ሰዳችሁ፥ በፍቅርም ታንጻችሁ ክርስቶስ በልባችሁ በእምነት እንዲኖር፥


እነርሱም በበጉ ደምና በምስክራነታቸው ቃል ድል ነሡት፤ ሞትን እስኪሸሹ ድረስ ነፍሳቸውንም አልወደዱም።


ትእዛዙን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በእኛ እንደሚኖር በዚህ እናውቃለን፥ ይኸውም በሰጠን በመንፈሱ ነው።


አሁን የዚህ ዓለም ፍርድ ደርሶአል፤ አሁን የዚህ ዓለም ገዥ ወደ ውጭ ይጣላል፤


ይህም እኔ በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በፍጹም አንድ እንዲሆኑ፥ እንዲሁም አንተ እንደ ላክኸኝና በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ዓለም እንዲያውቅ ነው።


እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም። በዚህም የእውነትን መንፈስና የስሕተትን መንፈስ እናውቃለን።


የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥ በእነርሱ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።


አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችሁታልና እጽፍላችኋለሁ። ወጣቶች ሆይ፥ ክፉውን አሸንፋችሁታልና እጽፍላችኋለሁ።


“ምግብ ለሆድ ነው፤ ሆድም ለምግብ ነው፤” እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሰውነት ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሰውነት ነው፤


በዚህም የዚህን ዓለም አኗኗር በመከተል፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው፥ በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ እየታዘዛችሁ ትኖሩ ነበር።


ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።


እንደ እነርሱ ከሆነ የማያምኑ ሰዎችን ልቦና፥ የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ አሳውሯል።


ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፤ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም ምንም ኃይል የለውም፤


ልጆቼ ሆይ፥ ይህን የምጽፍላችሁ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ብዬ ነው። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።


ልባችን ቢወቅሰን እንኳ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios