በስልቻዎቻቸው እህል እንዲሞሉላቸው፤ ብሩንም በያንዳንዱ ሰው ስልቻ ውስጥ መልሰው እንዲያስቀምጡና ለጉዞአቸው ስንቅ እንዲያሲዟቸው ዮሴፍ ትእዛዝ ሰጠ። ይህም ከተደረገላቸው በኋላ፥
ሮሜ 12:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለማንም በክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር አስቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለማንም ክፉን በክፉ አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ትጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር አድርጉ እንጂ፥ ሰዎች ክፉ ነገር ሲያደርጉባችሁ፥ እናንተም መልሳችሁ ክፉ ነገር አታድርጉባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉ ላደረገባችሁም ክፉ አትመልሱለት፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎውን ተነጋገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ። |
በስልቻዎቻቸው እህል እንዲሞሉላቸው፤ ብሩንም በያንዳንዱ ሰው ስልቻ ውስጥ መልሰው እንዲያስቀምጡና ለጉዞአቸው ስንቅ እንዲያሲዟቸው ዮሴፍ ትእዛዝ ሰጠ። ይህም ከተደረገላቸው በኋላ፥
“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ” ተብሎ ተጽፎአልና፥ ተወዳጆች ሆይ! ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ለቁጣው ቦታ ስጡ እንጂ።
እንግዲህ ወጣት መበለታት እንዲያገቡ፥ ልጆችንም እንዲወልዱ፥ እያንዳንዳቸውም ቤተሰቦቻቸውን እንዲያስተዳድሩ እፈቅዳለሁ፤ በዚህም ተቃዋሚ የሚሳደብበትን ምንም ዓይነት ሰበብ እንዳይሰጡት ነው፤
ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር በሚጎበኝበት ቀን፥ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ እርሱን እንድያከብሩት በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።
ነገር ግን በገርነትና በአክብሮት አድርጉት፤ በክርስቶስ ያላችሁን መልካም ጠባይ በመንቀፍ የሚናገሩ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ መልካም ሕሊና ይኑራችሁ።
እስኪነጋም በእግርጌው ተኛች፥ ቦዔዝም፦ “ሴት ወደ አውድማው እንደ መጣች ማንም እንዳያውቅ” ብሎ ነበርና ማንም ሊያያት በማይችልበት ሰዓት በማለዳ ከመኝታዋ ተነሣች።