በክፉ በሽታ ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም አይቀበሩምም፥ በመሬትም ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ፤ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፥ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።
ራእይ 19:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባርያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ ትበሉ ዘንድ” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትሰበሰቡትም የነገሥታትን ሥጋ፣ የጦር አዛዦችን ሥጋ፣ የብርቱ ሰዎችን ሥጋ፣ የፈረሶችንና የፈረሰኞችን ሥጋ እንዲሁም የሰዎችን ሁሉ፣ ይኸውም የጌቶችንና የባሮችን፣ የታናናሾችንና የታላላቆችን ሥጋ እንድትበሉ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የነገሥታትን ሥጋ፥ የጦር አዛዦችን ሥጋ፥ የብርቱ ጦረኞችን ሥጋ፥ የፈረሶችንና የፈረሰኞችን ሥጋ፥ የጌቶችንና የአገልጋዮችን ሥጋ፥ የታናናሾችንና የታላላቆችን ሥጋ፥ የማንኛውንም ሰው ሁሉ ሥጋ ኑ ብሉ!” |
በክፉ በሽታ ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም አይቀበሩምም፥ በመሬትም ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ፤ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፥ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።
በዚህም ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምክር አፈርሳለሁ፥ በጠላቶቻቸውም ፊት በሰይፍና ነፍሳቸውን በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ፥ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ።
አንተንና የወንዞችህን ዓሦች ሁሉ ወደ ምድረ በዳ እጥላለሁ፤ በሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤ አትከማችም፥ አትሰበሰብም፤ ምግብ እንድትሆን ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች እሰጥሃለሁ።
አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለሚበርሩ ወፎች ሁሉ፥ ለምድር አራዊት ሁሉ እንዲህ በላቸው፦ ኑ፥ ተሰብሰቡ፥ በእስራኤል ተራሮች ላይ ወደማርድላችሁ መሥዋዕቴ፥ ወደ ታላቁ መሥዋዕት ከየስፍራው ተሰብሰቡ፥ ሥጋንም ትበላላችሁ ደምንም ትጠጣላችሁ።
አሕዛብም ተቈጡ፤ ቁጣህም መጣ፤ በሙታንም የምትፈርድበት ዘመን መጣ፤ ለባርያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን፥ ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን የምትሰጥበት ምድርንም የሚያጠፉትን የምታጠፋበት ዘመን መጣ።”
ያየሃቸውም ዐሥር ቀንዶችና አውሬው አመንዝራይቱን ይጠላሉ፤ ይበዘብዟታል፥ ራቁትዋንም ያደርጓታል፤ ሥጋዋንም ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል።
የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም፥ ሀብታሞችም፥ ኃይለኞችም፥ አገልጋዮችም፥ ጌቶችም ሁሉ በዋሻዎችና በተራራዎች ዐለቶች ውስጥ ተሰወሩ፤
ጌታ ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እኔ መትቼ እጥልሃለሁ፤ ራስህንም እቆርጠዋለሁ። በዚህች ዕለት የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ሬሣ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፤ ዓለምም ሁሉ በእስራኤል ዘንድ እግዚአብሔር መኖሩን ያውቃል።