ራእይ 14:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ለማብሰር ዘላለማዊውን ወንጌል የያዘ ሌላ መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሌላ መልአክ በሰማይ መካከል ሲበርር አየሁ፤ እርሱም በምድር ላይ ለሚኖሩ ለሕዝብ፣ ለነገድ፣ ለቋንቋና ለወገን ሁሉ የሚሰብከውን የዘላለም ወንጌል ይዞ ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ በምድር ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ፥ ነገድ፥ ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን ለሚናገሩና ለተለያዩ ወገኖች ሁሉ ለማብሠር ዘለዓለማዊውን ወንጌል የያዘ ሌላ መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤ |
ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፥ ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ፥ መዳኔን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፥ መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን? በውኑ ቤቴ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ አይደለምን?
ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንሡ፥ ወደ ታችም ወደ ምድር ተመልከቱ፤ ሰማያትን እንደ ጢስ በንነው ይጠፋሉ፥ ምድርም እንደ ልብስ ታረጃለች፥ የሚኖሩባትም እንዲሁ ይሞታሉ፤ ማዳኔ ግን ለዘለዓለም ይሆናል፥ ጽድቄም አይፈርስም።
ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ስድስት ክንፍ ነበራቸው። በሁለት ክንፍ ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለት ክንፍ እግራቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፍ ይበሩ ነበር፤
ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት የምትጸኑ ከሆነ ነው፤ ይህም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፤ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ።
ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ለመንፋት የተዘጋጀው መልአክ የመለከቱን ድምፁም በሚያሰማባቸው ቀኖች፥ የእግዚአብሔር ምሥጢር ለባርያዎቹ ለነቢያት የምሥራች በሰበከላቸው መሠረት ይፈጸማል፤” አለ።
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።
አየሁም፤ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “የቀሩት ሦስቱ መላእክት መለከትን በሚነፋበት ጊዜ ከሚቀረው ድምፅ የተነሣ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!”