ሮሜ 16:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 እንግዲህ በወንጌሌ፥ በኢየሱስ ክርስቶስም ስብከት፥ ለዘመናት ተሰውሮ በነበረው የምሥጢር ግልፀት ሊያጸናችሁ ለሚችለው ለእርሱ፥ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም25-26 በዘላለማዊ አምላክ ትእዛዝ ሕዝቦች ሁሉ አምነው እንዲታዘዙ፣ በነቢያት መጻሕፍት አሁን በተገለጠው፣ ላለፉት ረዥም ዘመናት ተሰውሮ በነበረው ምስጢር መገለጥ መሠረት፣ በአስተማርሁት ወንጌልና በኢየሱስ ክርስቶስ መሰበክ ሊያጸናችሁ ለሚችለው፣ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 እኔ በማበሥረው የምሥራች ቃል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚተላለፈው መልእክትና ከጥንት ዘመን ጀምሮ ተደብቆ በቈየው፥ አሁን ግን በተገለጠው የእውነት ምሥጢር አማካይነት እርሱ በእምነታችሁ እንድትቆሙ ሊያደርጋችሁ ይችላል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 ይህም በነቢያት ቃልና የዘለዓለም ገዥ በሚሆን በእግዚአብሔር ትእዛዝ በዚህ ወራት ተገለጠ፤ አሕዛብ ሁሉ ይህን ሰምተውና ዐውቀው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25-26 እንግዲህ እንደ ወንጌል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መጻሕፍት የዘላለም እግዚአብሔር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምሥጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው፥ Ver Capítulo |