Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ጴጥሮስ 1:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 የጌታ ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።” የተሰበከላችሁም የምሥራች ቃል ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” የተሰበከላችሁም የምሥራች ቃል ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 የጌታ ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።” የተሰበከላችሁም የምሥራች ቃል ይኸው ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል።” በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar




1 ጴጥሮስ 1:25
23 Referencias Cruzadas  

ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ የአምላካችን ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንታ ትኖራለች።


እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ከሕግ አንዲት ኢዮታ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም።


አቤቱ፥ ቃልህ በሰማይ ለዘለዓለም ይኖራል።


ከመጀመሪያው የነበረውን፥ የሰማነውን፥ በዐይኖቻችንም ያየነውን፥ የተመለከትነውንና እጆቻችንም የዳሰሱትን፥ ስለ ሕይወት ቃል እንናገራለን፤


ደግሞም ይህን የበለጠ የሚያረጋግጥ የነቢያት ቃል አለ፤ ጎሕ እስኪቀድ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪገለጥ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚያስተውል ቃሉን ልብ በማለት መልካም ታደርጋላችሁ።


ዘመኖቼ እንደ ጥላ አዘንብለዋል፥ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።


ነገር ግን ከሕግ አንዲት ነጥብ ከምትወድቅ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል።


መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን ሰበከ፤


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በእኛም ዘንድ አደረ፤ ጸጋንና እውነትን የተመላውን፥ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ ያለውን ክብሩንም አየን።


በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።


አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው።


እናንተም ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን እንነግራችኋለን። ኅብረታችንም ከአብና ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።


ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ፥ አዲስ እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹሑን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤


ዳግመኛ የተወለዳችሁት በሕያውና ጸንቶ በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት ከማይጠፋ ዘር እንጂ፤ ከሚጠፋ ዘር አይደለም።


ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን በነገሯችሁ ነገር፥ እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፥ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።


ተገቢም በሆነው በራሱ ጊዜ፥ በአዳኛችን በእግዚአብሔር ትእዛዝ፥ ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት አማካይነት ቃሉን ገለጠ፤


ከቅዱሳን ሁሉ ያነስኩ ብሆንም፥ ወሰን የሌለውን የክርስቶስን ባለጠግነት ለአሕዛብ እንድሰብክ፥ ይህ ጸጋ ለኔ ተሰጠ፤


በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር፥ እርሱም እንደ ተሰቀለ፥ ሌላ ነገር ላለማወቅ ወስኜ ነበርና።


አንድ ድምጽ “ጩኽ!” አለኝ፤ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልኩ። ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው።


መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና መጪውንም የዓለም ኃይል የቀመሱ፥


በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ለማብሰር ዘላለማዊውን ወንጌል የያዘ ሌላ መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios