La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 83:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቤቱ፥ በጸጥታ አትቆይ፥ አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጠላቶችህ እንዴት እንደ ተነሣሡ፣ ባላንጣዎችህም እንዴት ራሳቸውን ቀና ቀና እንዳደረጉ ተመልከት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነሆ፥ ጠላቶችህ ዐምፀዋል፤ የሚጠሉህ ሁሉ ራሳቸውን በአንተ ላይ አንሥተዋል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤቱ፥ ነፍሴ አደ​ባ​ባ​ዮ​ች​ህን በመ​ው​ደድ ደስ አላት፤ ልቤም ሥጋ​ዬም በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ አላ​ቸው።

Ver Capítulo



መዝሙር 83:2
22 Referencias Cruzadas  

በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህ ልጓም አድርጌ፥ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”


ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር። አምላክ ሆይ፥ ምስጋናዬን ዝም አትበል፥


የጠላቶችህን ቃል አትርሳ፥ የተቃዋሚዎችህ ድንፋታ ሳያቋርጥ ወደ አንተ ይወጣል።


ጠላቶችህ በአደባባይህ ላይ አገሡ፥ ለድል ምልክት ዐላማቸውን አኖሩ።


ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባዋረድኋቸው ነበር፥ በሚያስጨንቋቸውም ላይ እጄን በጣልሁ ነበር፥


አቤቱ፥ ወንዞች ከፍ ከፍ አደረጉ፥ ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ ከፍ አደረጉ።


እንደ ባሕር ሞገድ ለሚተም የብዙ ሕዝቦች ጩኸት፥ እንደ ኃያል የውኃ ሞገድ የሚያስገመግም ድምጽ ለሚያሰሙ ሕዝቦች ወዮላቸው!


የተገዳደርኸው የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደርግህበት፥ ዓይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ አይደለምን!’


ቁጣህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ።


ከአንተም ጋር ይዋጋሉ፥ ነገር ግን አንተን ላድንህ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ድል አይነሡህም፥ ይላል ጌታ።”


ጲላጦስም ይህ ነገር ሁከት ከማስነሳት በስተቀር ምንም እንደማይጠቅም ባየ ጊዜ፥ ውሃ ወስዶ “እኔ ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ ጉዳዩ የእናንተ ነው፤” ብሎ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።


ሕዝቡም አብረው ተነሡባቸው፤ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ፤


አይሁድ ግን ቀንተው ከሥራ ፈቶች ክፉ ሰዎችን አመጡ ሕዝብንም ሰብስበው ከተማውን አወኩ፤ ወደ ሕዝብም ያወጡአቸው ዘንድ ፈልገው ወደ ኢያሶን ቤት ቀረቡ፤


ከተማውም ሁሉ ታወከ፤ ሕዝቡም ሁሉ ተሰበሰቡ ጳውሎስንም ይዘው ከመቅደስ ውጭ ጎተቱት፤ ወዲያውም ደጆች ተዘጉ።


እስከዚህም ቃል ድረስ ይሰሙት ነበር፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው፥ “እነደዚህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው፤ በሕይወት ይኖር ዘንድ አይገባውምና፤” አሉ።


ብዙ ጥልም በሆነ ጊዜ የሻለቃው ጳውሎስን እንዳይገነጣጥሉት ፈርቶ ጭፍሮቹ ወርደው ከመካከላቸው እንዲነጥቁት ወደ ሰፈሩም እንዲያገቡት አዘዘ።


ስለዚህ ምድያማውያን በእስራኤላውያን ተሸነፉ፤ ዳግመኛም ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም። ጌዴዎን በሕይወት እስካለ ጊዜ ድረስ ምድሪቱ አርባ ዓመት ሰላም አገኘች።