መዝሙር 77:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዱሮውን ዘመን አሰብሁ፥ የጥንቱን ዓመታት አሰብሁ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዝማሬዬን በሌሊት አስታወስሁ፤ ከልቤም ጋራ ተጫወትሁ፤ መንፈሴም ተነቃቅቶ እንዲህ ሲል ጠየቀ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሊቱን የማነጋው በጥልቅ ሐሳብ ነው፤ ሳሰላስል ሳለሁ ራሴን የምጠይቀው እንዲህ እያልኩ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚመጣ ትውልድ የሚወለዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ ተነሥተውም ለልጆቻቸው ይነግራሉ። |
ነገር ግን፦ በሌሊት የደስታ መዝሙሮችን የሚለግስ፥ ከምድርም እንስሶች ይልቅ የሚያስተምረን ከሰማይም ወፎች ይልቅ ጥበበኞች የሚያደርገን ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ወዴት ነው? የሚል የለም።
እኔ በልቤ፦ እነሆ፥ ከእኔ አስቀድመው በኢየሩሳሌም ላይ ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ጥበብን አብዝቼ ጨመርሁ፥ ልቤም ብዙ ጥበብንና እውቀትን ተመለከተ ብዬ ተናገርሁ።
“የቀድሞውን ዘመን አስታውስ፤ የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፥ አባትህን ጠይቅ፥ እርሱም ያስታውቅሃል፥ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ እነርሱም ይነግሩሃል።