መዝሙር 72:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘለዓለም ይባረክ፥ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። አሜን፥ አሜን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክቡር ስሙ ለዘላለም ይባረክ፤ ምድርም ሁሉ በክብሩ ትሞላ። አሜን፤ አሜን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክቡር ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን! ክብሩ በምድር ሁሉ ይሙላ! አሜን! አሜን! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ፥ ስለ ኀጢአታቸውም ጠፉ። |
ሌዋውያኑ ኢያሱ፥ ቃድምኤል፥ ባኒ፥ ሐሻብንያ፥ ሼሬብያ፥ ሆዲያ፥ ሽባንያ፥ ፕታሕያ እንዲህ አሉ፦ “ቁሙ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ጌታ አምላካችሁን ባርኩ። ከበረከትና ከምስጋና ሁሉ በላይ ከፍ ያለው የክብርህን ስም ይባርኩ።
ነቢዩም ኤርምያስ እንዲህ አለ፦ “አሜን፥ ጌታ እንዲህ ያድርግ፤ የጌታን ቤት ዕቃዎችና ምርኮውን ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ በመመለስ ጌታ የተናገርኸውን የትንቢት ቃላት ይፈጽም።
“ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፤ በሁሉም ስፍራ ለስሜ ዕጣን ያመጣሉ፥ ንጹሕ ቁርባንም ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፥” ይላል የሠራዊት ጌታ።
በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ “ውዳሴ ገናናነት ክብርም ኃይልም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን፤” ሲሉ ሰማሁ።