መዝሙር 64:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንደበታቸው ያሰናክላቸዋል፥ የሚያዩአቸውም ሁሉ ይደነግጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰው ልጆች ሁሉ ይፈራሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ በይፋ ያወራሉ፤ ያደረገውንም በጥሞና ያሰላስላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ሁሉ ይፈራሉ፤ ስለ እግዚአብሔር ሥራ ይናገራሉ፤ ስላደረገውም ነገር ያሰላስላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድርን ጐበኘሃት አረካሃትም፥ ብልጽግናዋንም እጅግ አበዛህ፤ የእግዚአብሔር ወንዝ ውኆችን የተመላ ነው፤ ምግባቸውን አዘጋጀህ፥ እንዲሁ ታሰናዳለህና። |
በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፤ ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ ነገር ግን ለጌታ ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም።
የአምላካችንን የጌታን በቀል ስለ መቅደሱም ሲል የሚበቀለውን በቀል በጽዮን ለመናገር ከባቢሎን ምድር የሚመጡትን የኰብላዮችና የስደተኞች ድምፅ አድምጡ።
ኤፍሬም ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ከጣዖታት ጋር እኔ ምን አደርጋለሁ? እኔ እመልስለታለሁ፥ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፤ እኔ እንደ ለመለመ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህ በእኔ ዘንድ ይገኛል።
በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።