Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 14:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 መንገዳቸውንና ሥራቸውን ባያችሁ ጊዜ ያጽናኑአችኋል፥ ያደረግሁትም ሁሉ በከንቱ እንዳላደረግሁት ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አካሄዳቸውንና ተግባራቸውን በምታዩበት ጊዜ፣ ትጽናናላችሁ፤ አንዳች ነገር በከንቱ እንዳላደረገሁ ትረዳላችሁና፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንና ሥራ​ቸ​ውን በአ​ያ​ችሁ ጊዜ ያጽ​ና​ኗ​ች​ኋል፤ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ት​ንም ሁሉ በከ​ንቱ እን​ዳ​ላ​ደ​ረ​ግ​ሁ​ባት ታው​ቃ​ላ​ችሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 መንገዳቸውንና ሥራቸውን ባያችሁ ጊዜ ያጽናኑአችኋል፥ ያደረግሁባትንም ሁሉ በከንቱ እንዳላደረግሁባት ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 14:23
20 Referencias Cruzadas  

በደረሰብንም ነገር ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ፥ አንተ እውነት አድርገሃልና፥ እኛም ኃጢአት አድርገናል።


እርሱም በሰው ፊት እየዘመረ፦ እኔ በድያለሁ፥ ቀናውንም አጣምሜአለሁ፥ የሚገባኝንም ቅጣት አልተቀበልሁም፥


ወዲያና ወዲህ እንደሚበርር ድንቢጥ ወይም ጨረባ፥ እንዲሁም ከንቱ እርግማን በማንም ላይ አይደርስም።


የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


ለእነርሱ መጽናናት ስለሆንሻቸው እፍረትን እንድትሸከሚና በሠራሽውም ሁሉ እንድታፍሪ ነው።


ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ሲኦል በጣልሁት ጊዜ ከመውደቁ ድምፅ የተነሣ ሕዝቦችን አንቀጠቀጥሁ፤ ውኃ የሚጠጡ ሁሉ፥ ምርጦችና መልካሞች የሊባኖስ ዛፎች፥ የዔድን ዛፎች ሁሉ በታችኛው ምድር ውስጥ ተጽናንተዋል።


ንጉሡ ያለቅሳል፥ ልዑሉም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድሪቱም ሕዝቦች እጆች ይንቀጠቀጣሉ፥ እንደ መንገዳቸው መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


“ነገር ግን እኔን በመቃወም ሄደዋልና፥ በእኔ ላይ ፈጽሞ በከዳተኝነት ያደረጉትን በደላቸውንና የአባቶቻቸውን በደል ይናዘዛሉ።


እኔም ደግሞ እነርሱን በመቃወም እሄዳለሁ፤ ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አመጣቸዋለሁ፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የበደላቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥


ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሓ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቁጣ ቀን በራስህ ላይ ቁጣን ታከማቻለህ።


ጌታ አምላክህ ሊያስጨንቅህ፥ ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ፥ በልብህ ያለውን ያውቅ ዘንድ ሊፈትንህ፥ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስታውስ።


የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፤ የሚገባቸው ነውና፤”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos