እንደሚፈስስ ውኃ ይጥፉ፥ ቀስትን ሲገትሩ ፍላጻው ይጣመም።
ሲሄድ እንደሚቀልጥ ቀንድ አውጣ ይሁኑ፤ ፀሓይን እንደማያይ ጭንጋፍ ይሁኑ።
እየሄደ ሟምቶ እንደሚያልቅ ቀንድ አውጣና ሞቶ እንደ ተወለደና ብርሃንን ከቶ እንዳላየ ጭንጋፍ ይሁኑ።
የምትሰማቸው አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥቅባቸዋለህ፥ አሕዛቡንም ሁሉ ትንቃቸዋለህ፥
እንዳልነበረ በሆንሁ፥ ከማኅፀንም ወደ መቃብር በወሰዱኝ።
ወይም እንደ ተደበቀበ ጭንጋፍ፥ ብርሃንም እንዳላዩ ሕፃናት በሆንሁ ነበር።
ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ነገር ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ።
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።
ሀብታምም እንደ ሣር አበባ ስለሚረግፍ በውርደቱ ይመካ።