መዝሙር 58:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል፥ በክፉዉም ደም እግሮቹን ይታጠባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎችም፣ “በርግጥ ለጻድቃን ብድራት ተቀምጦላቸዋል፤ በእውነትም በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ” ይላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ሰዎች “ጻድቃን የመልካም ሥራቸውን ዋጋ አገኙ፤ በዓለም ላይ የሚፈርድ አምላክ በእርግጥ አለ” ይላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፤ አቤቱ፥ አምላኬና ረዳቴ፥ በኀይልህ በትናቸው፥ አዋርዳቸውም። |
በቃላችሁ ጌታን አሰልችታችሁታል። እናንተም፦ እርሱን ያሰለቸነው በምንድን ነው? ትላላችሁ። “ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በጌታ ፊት መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል” ወይም “የፍትሕ አምላክ የት አለ?” በማለታችሁ ነው።
እናንተም እንዲህ ብላችኋል፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ ትእዛዙን መጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ ፊት ኀዘንተኞች ሆነን መሄድ ምን ይጠቅመናል?