ሆኖም ወደ አባቶቹ ትውልድ ይወርዳል፥ ለዘለዓለም ብርሃንን ወደ ማያዩበት።
ሰው በሀብቱ እንደ ተከበረ አይዘልቅም፤ ታይተው የሚጠፉ እንስሳትን ይመስላል።
ያለ ማስተዋል ሀብት ያካበተ ሰው እንደ እንስሳ መሞቱ አይቀርም።
ተቀምጠህ ወንድምህን ታማዋለህ፥ ለእናትህም ልጅ ዕንቅፋትን አኖርህ።
ወደማልመለስበት ስፍራ ሳልሄድ፥ ወደ ጨለማና ወደ ሞት ጥላ ምድር፥
ገመዳቸው የተነቀለ አይደለምን? አለጥበብም ይሞታሉ።’”
ብዙ መሬት በስማችው ቢያስጠሩም እንኳን፥ መቃብራቸው የዘለዓለም ቤታቸው፥ ለልጅ ልጅ የሚሆን ማደሪያቸውም ነው።
ሰው ብዙ ዘመን በሕይወት ቢኖር በሁሉም ደስ ይበለው፥ ሆኖም የጨለማውን ዘመን ያስብ፥ ብዙ ቀን ይሆናልና። የሚመጣው ነገር ሁሉ ከንቱ ነው።