መዝሙር 47:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቦች ሁላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር እልል በሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቦች ሁሉ፥ በደስታ አጨብጭቡ! ከፍ ባለ ድምፅ በመዘመር፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ በአምላካችን ከተማ በመቅደሱ ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው። |
ከዚያም በኋላ ዮዳሄ ኢዮአስን አውጥቶ በራሱ ላይ ዘውድ ጫነበት፤ ለመንግሥቱ መመሪያ የሆነውንም ሕግ አንድ ቅጂ አስረከበው፤ በዚህ ዓይነት ኢዮአስ ተቀብቶ ነገሠ፤ ሕዝቡም እያጨበጨበ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ!” አለ።
ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ስለ ያዕቆብ በደስታ ዘምሩ ስለ አሕዛብም አለቆች እልል በሉ፤ አውጁ፥ አመስግኑ፦ ጌታ ሆይ! ሕዝብህን የእስራኤልን ትሩፍ አድን በሉ።
ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎችም፦ ‘ሞገስ ይሁንለት! ሞገስ ይሁንለት!’ ብለው እየጮኹ እርሱ የመደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል” ብሎ ነገረኝ።
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ! አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ! እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።
ሳሙኤልም መላውን ሕዝብ፥ “ጌታ የመረጠውን ሰው አያችሁን? ከሕዝቡ ሁሉ የሚስተካከለው ማንም የለም” አለ። ከዚያም ሕዝቡ፥ “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ ይሁን!” ብሎ ጮኸ።