በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን፥ በስምህም የሚነሡብንን እንረግጣለን።
በቀስቴ አልተማመንም፤ ሰይፌም አያስጥለኝም።
በቀስቴ አልተማመንም፤ ሰይፌም አያድነኝም።
አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘለዓለም ነው፤ በትረ መንግሥትህ የጽድቅ በትር ነው።
ጌታ የቀባውን እንዳዳነው ዛሬ አወቅሁ፥ ከሰማይ መቅደሱ ይመልስለታል፥ በቀኙ ብርታት ማዳን አለና።
እንዲህም ሆነ ሙሴ እጁን ባነሣ ጊዜ እስራኤል ይበረታ ነበር፤ እጁንም ባወረደ ጊዜ አማሌቅ ይበረታ ነበር።
ነገር ግን የይሁዳን ቤት እምራለሁ፤ እነርሱንም በቀስት ወይም በሰይፍ ወይም በጦርነት ወይም በፈረሶች ወይም በፈረሰኞች ሳይሆን በአምላካቸው በጌታ አድናቸዋለሁ።”
እዚህ የተሰበሰቡትም ሁሉ ጌታ ያለ ሰይፍ ወይም ያለ ጦር እንደሚያድን ያውቃሉ፤ ሰልፉ የጌታ ስለ ሆነም ሁላችሁን በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል።”