መዝሙር 4:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች፥ የዳዊት መዝሙር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽድቄ አምላክ ሆይ፤ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፤ ከጭንቀቴ አሳርፈኝ፤ ማረኝ፤ ጸሎቴንም ስማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ የእውነት አምላክ ነህ፤ እባክህን ለጸሎቴ መልስ ስጠኝ! እኔ በጣም በጭንቀት ላይ ነበርኩ አንተ ግን ነጻ አወጣኸኝ፤ አሁንም ራራልኝና ጸሎቴን ስማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን በጠራሁት ጊዜ ጽድቄን ሰማኝ፥ ከጭንቀቴም አሰፋልኝ፤ ይቅር አለኝ፥ ጸሎቴንም ሰማኝ። |
ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎቼም ላይ ያስሄደኛል። ለመዘምራን አለቃ፥ በባለ አውታር መሣሪያዎቼ።
ወንድሞች ሆይ! በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን ብታውቁት እንወዳለን፤ በሕይወታችን ተስፋ እስክመቁረጥ የሚያደርስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር።
ከአንበሳ መዳፍና ከድብ መንጋጋ ያዳነኝ ጌታ አሁንም ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሲል ዳዊት ተናገረ። ሳኦልም ዳዊትን፥ “ሂድ፤ ጌታ ካንተ ጋር ይሁን!” አለው።