ጌታ ግን ይሥቅበታል፥ ቀኑ እንደሚደርስ አይቶአልና።
እግዚአብሔር ግን ይሥቅባቸዋል፣ ቀናቸው እንደ ደረሰ ያውቃልና።
ክፉዎች ሰዎች የሚጠፉበት ቀን እንደ ተቃረበ ስለሚያውቅ እግዚአብሔር በእነርሱ ይስቃል።
እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቆሮ፥ አፉንም እንደማይከፍት ዲዳ ሆንሁ።
የፊተኞች ሰዎች እንደ ደነገጡ፥ እንዲሁ የኋለኞች ሰዎች ስለ ዘመኑ ይደነቃሉ።
በሰማያት የሚቀመጠውም እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።
እኔም በእናንተ መጥፋት እስቃለሁ፥ ሽብር በመጣባችሁ ጊዜ አላግጥባችኋለሁ
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እብሪተኛውንና ትዕቢተኛውን ሁሉ፤ የተኩራራውን በሙሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።
ወይፈኖችዋን ሁሉ እረዱ፥ ወደ መታረድም ይውረዱ፤ ቀናቸው፥ የመጐብኘታቸው ጊዜ ደርሶአልና ወዮላቸው!
አንተም ቀንህ የደረሰብህ፥ የኃጢአትህ ቀጠሮ ጊዜ የደረሰብህ፥ ርኩስ ኃጢአተኛ የእስራኤል አለቃ ሆይ፥
አንገት ላይ ያኖሩህ ዘንድ ከንቱን ራእይ ነገር ሲያዩልህ በሐሰትም ምዋርት ሲናገሩልህ፦ ሰይፍ፥ ሰይፍ ተመዝዞአል፥ ይገድልም ዘንድ ያብረቀርቅም ዘንድ ተሰንግሎአል በል።
ሕያው ጌታ አለ፥ ጌታ ራሱ ይቀሥፈዋል፤ ወይም የመሞቻው ቀን ይመጣል፤ ወይም በጦርነት ይሞታል፤ ይጠፋልም።