ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ለዘላለሙ ትረሳኛለህ? ፊትህንስ ከእኔ የምትሰውረው እስከ መቼ ድረስ ነው?
እግዚአብሔር ሆይ፥ እስከ መቼ ትረሳኛለህ? የምትረሳኝ ለዘለዓለም ነውን? እስከ መቼስ ከእኔ ትሰወራለህ?
ሰነፍ በልቡ፥ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐሰቈሉም፤ በጎ ነገርን የሚሠራት የለም። አንድም እንኳ የለም።
ፊትህን ለምን ትሰውራለህ? እንደ ጠላትህም የቈጠርኸኝ ለምንድነው?
አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ተነሥ እጅህንም ከፍ ከፍ አድርግ፥ ድሆችን አትርሳ።
አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ዝም ብለህ ታየኛለህ? ነፍሴን ከክፉ ሥራቸው ብቸኛዪቱንም ከአንበሶች አድናት።
አቤቱ፥ ንቃ፥ ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፥ ለዘወትርም አትጣለን።
ዝያለሁና አቤቱ፥ ማረኝ፥ አጥንቶቼ ታውከዋልና ፈውሰኝ።
የአሳፍ ትምህርት። አቤቱ፥ ስለምን ለሁልጊዜ ጣልኸኝ? በማሰማርያህ በጎች ላይስ ቁጣህ ስለምን ጨሰ?
አቤቱ፥ መልሰን፥ ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።
የመድኃኒታችን አምላክ ሆይ፥ መልሰን፥ ቁጣህንም ከእኛ መልስ።
ዕድሜውንም አሳጠርህ፥ በእፍረትም ሸፈንኸው።
በማለዳ ጽኑ ፍቅርህን እንጠግባለን፥ በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን።
ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል የመለያያ አጥር ሆናለች፤ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።
ስለምን ለዘለዓለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?
በዚያች ቀን እቀጣቸዋለሁ፤ እተዋቸዋለሁም፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይጠፋሉ። ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር ይደርስባቸዋል፤ በዚያችም ቀን፥ ‘ይህ ጥፋት የደረሰብን፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባለመሆኑ አይደለምን?’ ይላሉ።