ፀሐይ በቀን አይመታህም፥ ጨረቃም በሌሊት እንዲሁ።
ፀሓይ በቀን አያቃጥልህም፤ ጨረቃም በሌሊት ጕዳት አታመጣብህም።
ፀሐይ በቀን፥ ጨረቃም በሌሊት ጒዳት አያደርሱብህም።
የኢየሩሳሌም ደኅንነትዋን፥ ተነጋገሩ። ስምህን ለሚወድዱ ደስታቸው ነው።
የሚራራላቸውም ይመራቸዋልና፥ በውኃም ምንጮች በኩል ይነዳቸዋልና አይራቡም፥ አይጠሙም፥ የበረኅ ትኩሳት ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም።
ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።
ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፤ ከእንግዲህም ወዲህ አይጠሙም፤ ፀሐይም ሆነ ትኩሳትም ሁሉ ከቶ አይመታቸውም፤