መዝሙር 110:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንገድ ከፈሳሽ ውኃ ይጠጣል፥ ከዚህም የተነሣ ራሱን ከፍ ከፍ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንገድ ዳር ካለች ፈሳሽ ውሃ ይጠጣል፤ ስለዚህ ራሱን ቀና ያደርጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ከመንገድ ዳር ካለው ምንጭ ከጠጣ በኋላ፥ ኀይሉን በማደስ በድል አድራጊነት ጸንቶ ይቆማል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእጆቹ ሥራ እውነትና ቅን ነው፤ ትእዛዙም ሁሉ የታመነ ነው፥ |
እነሆ፥ አሁን በዙሪያ ባሉ በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፥ በድንኳኑም የእልልታ መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ ለጌታ እቀኛለሁ እዘምርለትማለሁ።
ስለዚህ ስለ ነብያት የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ከኢየሩሳሌም ነቢያት ዘንድ ርኩሰት በምድር ሁሉ ላይ ወጥቶአልና፥ እሬትን አበላቸዋለሁ የሐሞትንም ውኃ አጠጣቸዋለሁ።”
እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በዓሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያ አምስተኛው ቀን፥ የባቢሎን ንጉሥ ኤዌል ማሮዴክ በነገሠ በአንደኛው ዓመት ለይሁዳ ንጉሥ ለዮአኪን ቸርነት አደረገለት ከእስር ቤትም አወጣው፤
በእነርሱ ውስጥ የነበረው የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ እና ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ ሲመሰክር፥ ምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።
እግዚአብሔርም በሌሒ ዐለት ሰነጠቀለት፤ ከዚያም ውኃ ወጣ፤ ሳምሶንም ያን ሲጠጣ በረታ፤ መንፈሱም ታደሰ። ስለዚህ ያ ምንጭ ዓይንሀቆሬሸ ተባለ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያው በሌሒ ይገኛል።