መዝሙር 110:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ ብሎ”፥ ጌታ ማለ፥ አይጸጸትምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዐት፤ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ፣ እግዚአብሔር ምሏል፤ እርሱ ሐሳቡን አይለውጥም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር “በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘለዓለም ካህን ትሆናለህ” ብሎ ማለ፤ መሐላውም የማይሻር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጌትነቱ መታሰቢያን አደረገ፤ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው። |
እርሱ የጌታን መቅደስ ይሠራል፥ ክብርንም ይጐናጸፋል፥ በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ ይገዛል፤ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል ሰላማዊ መግባባት ይኖራል።
ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?
እንግዲህ በሌዊ ክህነት ፍጹምነት የተገኘ ከሆነ፥ ሕዝቡ በዚያ ላይ የተመሠረተን ሕግ ተቀብለዋልና፤ ወደ ፊት እንደ አሮን ሹመት የሚቆጠር ሳይሆን፥ እንደ መልከጼዴቅ ሹመት የሆነ ሌላ ካህን ሊነሣ ስለምን ያስፈልጋል?
እነዚያ ከዚህ በፊት ካህናት የሆኑት ያለ መሐላ ነው፤ እርሱ ግን ከመሐላ ጋር ካህን ሆኖአልና፤ “ጌታ ሐሳቡን አይቀይርም ‘አንተ እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ፤’ ብሎ ምሏል፥፥”