Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕብራውያን 7:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እነዚያ ከዚህ በፊት ካህናት የሆኑት ያለ መሐላ ነው፤ እርሱ ግን ከመሐላ ጋር ካህን ሆኖአልና፤ “ጌታ ሐሳቡን አይቀይርም ‘አንተ እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ፤’ ብሎ ምሏል፥፥”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እርሱ ግን ካህን የሆነው በመሐላ ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮለታል፤ “ጌታ ማለ፤ አሳቡንም አይለውጥም፤ ‘አንተ ለዘላለም ካህን ነህ።’ ”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ኢየሱስ ግን ካህን የሆነው በእግዚአብሔር መሐላ ነው፤ ይህም፦ “እግዚአብሔር ‘አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ’ ብሎ ምሎአል፤ አይለውጥም” ተብሎ በተነገረለት መሠረት ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በመ​ሐላ የሾ​መ​ውን ግን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ፥ አይ​ጸ​ጸ​ት​ምም፤ አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዘ​ለ​ዓ​ለም ካህን ነህ” አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 7:21
10 Referencias Cruzadas  

“እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ ብሎ”፥ ጌታ ማለ፥ አይጸጸትምም።


ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?


እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና።


እንደዚህም በሌላ ስፍራ ደግሞ “አንተ እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ” ይላል።


ስለ እርሱ “እንደ መልከጼዴቅ የክህነት ሹመት አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ” ተብሎ ተመስክሮለታል።


ከዚህም በቀር ይህ ክህነት ያለ መሐላ አልሆነም፤


በሞት ምክንያት በክህነት ሥራ ላይ ለመቆየት ስላልቻሉ፥ የቀድሞዎቹ ካህናት ቊጥራቸው ብዙ ነበር፤


ሕጉ ሰዎችን ድካም እያላቸው ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማል፤ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሐላው ቃል ግን፥ ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ሾመልን።


የእስራኤል ክብር የሆነው እርሱ አይዋሽም፤ አይጸጸትምም፤ እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos