እስራኤልን ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከድንኳን ወደ ድንኳን፥ ከማደሪያም ወደ ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርሁምና።
መዝሙር 11:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በተቀደሰው መቅደሱ ነው፥ ጌታ፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው፥ ዐይኖቹ ይመለከታሉ፥ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ የእግዚአብሔር ዙፋን በሰማይ ነው። ዐይኖቹ ሰዎችን ይመለከታሉ፤ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ ነው፤ ዙፋኑም በሰማይ ነው፤ የሰውን ልጆች ይመለከታል። አተኲሮም በማየት ዐይኖቹም ይመረምሩአቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ምላሳችንን እናበረታለን፤ ከንፈሮቻችን የእኛ ናቸው፥ ጌታችን ማን ነው?” የሚሉትን። |
እስራኤልን ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከድንኳን ወደ ድንኳን፥ ከማደሪያም ወደ ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርሁምና።
ጌታ ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ለማጽናት ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። እንግዲህ አሁን የሞኞችን ተግባር ፈጽመሃል። ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይደረግብሃል።”
እነሆ፥ እጄን በላያቸው ላይ አነሣለሁ፥ በምርኮ ተገዝተውላቸው ለነበሩት ራሳቸው በምርኮ ይዘረፋሉ፤ የሠራዊት ጌታም እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።
እርሱም ሰው የሚያመልከውን ነገር ወይም አማልክት ነን ከሚሉት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግና በመቃወም፦ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ብሎ ያውጃል፤ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ ይቀመጣል።