መዝሙር 103:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጎልማሳነትሽን እንደ ንስር ያድሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣ ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጐልማሳነቴ ሕይወቴን በመልካም ነገር ሁሉ ይሞላታል፤ እንደ ንስርም ወጣትነቴን ያድሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዘለዓለም እንዳትናወጥ፥ ምድርን መሠረታት፥ አጸናትም። |
በበኣሊም የበዓል ቀኖች ዕጣን ለእነርሱ በማጠንዋና ራስዋን በጉትቾችዋና በጌጥዋ በማስጌጥ ውሽሞችዋን ተከትላ እኔን በመርሳትዋ እቀጣታለሁ፥ ይላል ጌታ።
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ በሚያልፍም ባለጠግነት ላይ ሳይሆን እንድንደሰትበት ሁሉን አትረፍርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ እዘዛቸው።
ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ እንዲሁ ዛሬም ብርቱ ነኝ፤ ጉልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው።