በአልጋዬ ላይ ማለፊያ የአልጋ ልብስ ዘርግቼበታለሁ፥ የግብጽንም ያማሩ አልባሳት አንጥፌበታለሁ።
ዐልጋዬን ከግብጽ የመጣ፣ ጌጠኛ በፍታ አልብሼዋለሁ።
ከግብጽ አገር የመጣውን ጌጠኛ አንሶላ በአልጋዬ ላይ አንጥፌአለሁ።
በአልጋዬ ላይ ማለፊያ ሰርፍ ዘርግቼበታለሁ፥ የግብፅንም ሸመልመሌ ምንጣፍ።
ሰሎሞን ፈረሶችን ከግብጽና ከቀዌ ያስመጣ ነበር፤ የንጉሡም ነጋዴዎች ፈረሶችን በገንዘብ ገዝተው ከቀዌ ያመጡለት ነበር።
ለራስዋም የአልጋ ልብስ ትሠራለች ጥሩ በፍታና ቀይ ግምጃ ትለብሳለች።
ስለዚህ እንድገናኝህ፥ ፊትህንም በትጋት ለመሻት ወጥቻለሁ፥ አግኝቼሃለሁም።
ውዴ ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ውብ ነህ፥ መልከ መልካምም ነህ፥ አልጋችንም ለምለም ነው።
የተነደፈ የተልባ እግር ለሚፈትሉ፥ የተባዘተ ጥጥ የሚሰሩ ሸማኔዎችም ተስፋ ይቆርጣሉ።
ዓላማ ሆኖ እንዲያገለግልሽ፥ ሸራሽ ከግብጽ በፍታና ከወርቀ ዘቦ ተሠርቶአል፥ መደረቢያሽም ከኤሊሻ ደሴቶች የመጣ ሰማያዊና የወይን ጠጅ ነበር።
እነሆ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፤ ከእርሷም ጋር የሚያመነዝሩትንም ከሥራዋ ንስሓ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤