ሕዝቅኤል 27:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ዓላማ ሆኖ እንዲያገለግልሽ፥ ሸራሽ ከግብጽ በፍታና ከወርቀ ዘቦ ተሠርቶአል፥ መደረቢያሽም ከኤሊሻ ደሴቶች የመጣ ሰማያዊና የወይን ጠጅ ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 የመርከቦችሽ ሸራ ጥልፍ ሥራ ያለበት የግብጽ በፍታ ነበረ፤ ይህም እንደ ዐርማ አገለገለሽ። መጋረጃዎችሽ ከኤሊሳ ጠረፍ የመጡ፣ ባለሰማያዊና ሐምራዊ ቀለም ነበሩ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 የመርከብ ሸራሽ እንደ ዓላማ ሆኖ ከሩቅ ይታይ ዘንድ፥ በእጅ ሥራ ባጌጠ የግብጽ በፍታ ተሠርቶአል፤ መጋረጃዎችሽ ከቆጵሮስ ደሴት በተገኘ እጅግ በሚያምር ሰማያዊ ሐምራዊ ጨርቅ ተሠርቶአል፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ዓላማ እንዲሆንልሽ ሸራሽ ከግብፅ በፍታና ከወርቀ ዘቦ ተሠርቶአል፤ መደረቢያሽም ከኤሊሳ ደሴቶች ሰማያዊና ቀይ ሐር ተሠርቶአል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ዓላማ እንዲሆንልሽ ሸራሽ ከግብጽ በፍታና ከወርቅ ዘቦ ተሠርቶአል፥ መደረቢያሽም ከኤሊሳ ደሴቶች ሰማያዊና ቀይ ሐር ተሠርቶአል። Ver Capítulo |