ምሳሌ 7:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዘችውም ሳመችውም፥ ፊትዋም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አፈፍ አድርጋ ይዛ ሳመችው፤ ኀፍረቷንም ጥላ እንዲህ አለችው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያንን ወጣት ዕቅፍ አድርጋ ሳመችው፤ ያለ ኀፍረት እንዲህ አለችው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዘችውም ሳመችውም፤ ፊቷም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው፦ |
ለአመንዝራዎች ሁሉ ሥጦታ ይሰጡአቸዋል፥ አንቺ ግን ለወዳጆችሽ ሁሉ ሥጦታሽን ትሰጫለሽ፥ ለአመንዝራነትሽ ከየአቅጣጫው ወደ አንቺ እንዲገቡ ጉቦ ትሰጫቸዋለሽ።
ፊታቸው የተኮሳተረና ልባቸውም የደነደነ ልጆች ናቸው፥ እኔ ወደ እነርሱ እልክሃለሁ፥ አንተም እንዲህ በላቸው፦ “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤”
አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም፥ አትፍራ፥ ቃላቸውንም አትፍራ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቃላቸውን አትፍራ፥ ፊታቸውንም አትፍራው።
እነሆ፥ እነዚህ በፌጎር ምክንያት በበለዓም ምክር ጌታን አታልለው ለእስራኤል ልጆች ዕንቅፋት ሆኑ፤ በዚህም ምክንያት በጌታ ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆነ።
ዳሩ ግን ‘ነቢይ ነኝ’ የምትለውን፥ ባርያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ስለምትላት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤