Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 39:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እያደርም የጌታው ሚስት ዐይኗን ጣለችበት፤ አፍ አውጥታም፥ “አብረኸኝ ተኛ” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እያደርም የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዐይኗን ጣለች፤ አፍ አውጥታም፣ “ዐብረኸኝ ተኛ” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከጊዜ በኋላ የጌታው ሚስት ዮሴፍን ተመልክታ ስለ አፈቀረችው፥ “ና ከእኔ ጋር አብረን እንተኛ” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የጌ​ታው ሚስት በዮ​ሴፍ ላይ ዐይ​ን​ዋን ጣለ​ች​በት፤ “ከእ​ኔም ጋር ተኛ” አለ​ችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከዚህም በኍላ እንዲህ ሆነ የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዓይንዋን ጣለች፦ ከእኔም ጋር ተኛ አለችው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 39:7
19 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ምግቡን ስታቀርብለት አፈፍ አድርጎ ያዛትና፥ “እህቴ ነዪ አብረን እንተኛ” አላት።


ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትንም የማይተዉ ዐይኖች አላቸው፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው።


አመንዝራነትሽ ከሌሎች ሴቶች የተለየ ነው፥ ማንም ለዝሙት የሚከተልሽ የለም፤ ማንም ዋጋ ሳይሰጥሽ አንቺ ዋጋ ትሰጫለሽ፤ የተለየሽም ሆንሽ።


ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፥ የሥጋ ምኞት፥ የዐይን ምኞት፥ በኑሮ ደረጃ መመካት፥ ከዓለም ነው እንጂ ከአብ አይደለም።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወደ ሴት አይቶ የተመኛት ሁሉ ከወዲሁ በልቡ ከእርሷ ጋር አመንዝሮአል።


በባሏ ፋንታ ሌሎችን የምታስተናግድ አመንዝራ ሴት ሆነሻል።


“ከዐይኖቼ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ፥ እንግዲህ ቈንጆይቱን እንዴት በፍትወት እመለከታለሁ?


በየመንገዱ ራስ ሁሉ ላይ ከፍ ያለውን ቦታሽን ሠራሽ፥ ውበትሽንም አረከስሽ፥ ለአላፊ አግዳሚው ሁሉ እግርሽን ከፈትሽ፥ አመንዝራነትሽንም አበዛሽ።


ስለዚህ ካፊያ ተከለከለ፥ የበልጉም ዝናብ ጠፋ፤ የጋለሞታም ሴት ፊት ቢኖርሺም እንኳ ለማፈር ግን እንቢ አልሽ።


ያዘችውም ሳመችውም፥ ፊትዋም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው፦


ክብርህን ለሌላ እንዳትሰጥ፥ ዕድሜህንም ለጨካኝ፥


ከእንግዳይቱ ሴት አንተን ለመታደግ፥ ቃሏን ከምታለዝብ ከማትታወቀው ሴት፥


ከንቱ ነገርን እንዳያዩ ዐይኖቼን መልስ፥ በመንገድህ ሕያው አድርገኝ።


የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ፥ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።


ልጄ ሆይ፥ ኃጢአተኞች ቢያባብሉህ እሺ አትበል።


የሴተኛ ዐዳሪዋ ዋጋ እስከ አንዲት እንጀራ ነው፥ አመንዝራም ሴት የሰውን ሕይወት ታጠምዳለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios