ምሳሌ 6:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሰው ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፥ የሚነካትም ሁሉ ሳይቀጣ አይቀርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰው ሚስት ጋራ የሚተኛም እንደዚሁ ነው፤ የሚደርስባትም ከቅጣት አያመልጥም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ግንኙነት የሚያደርግ እንደዚሁ ነው፤ የሌላውን ሰው ሚስት የሚነካ ሁሉ ሳይቀጣ አይቀርም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ጐልማሳ ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፤ የሚነካትም ሁሉ አይነጻም። |
የሐዘኑ ጊዜ ካበቃ በኋላም፥ ዳዊት ልኮ ቤርሳቤህን ወደ ቤቱ አስመጣት፤ ሚስቱ ሆነች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት የሠራው ሥራ ጌታን አላስደሰተውም ነበር።
አኪጦፌልም መልሶ፥ “ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ አባትህ ከተዋቸው ዕቁባቶቹ ጋር ግባና ተኛ፤ ከዚያም አንተ፥ አባትህን እጅግ የጠላህ መሆንህን መላው እስራኤል ይሰማና አብሮህ ያለው ሁሉ ክንዱ ይበረታል” አለው።
“የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት፥ ወንድ ሠራተኛውን፥ ሴት ሠራተኛውን፥ በሬውን፥ አህያውን፥ የባልንጀራህ የሆነውን ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።”
ሰውም ከጎረቤቱ ሚስት ጋር ርኩሰትን አደረገ፥ ሌላውም የልጁን ሚስት በዝሙት አረከሰ፥ ሌላውም በአንቺ ውስጥ የአባቱን ልጅ፥ እኅቱን አዋረደ።
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።