ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም!
ምሳሌ 5:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ በክፋቱ ይጠመዳል፥ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉውን ሰው የገዛ መጥፎ ሥራው ያጠምደዋል፤ የኀጢአቱም ገመድ ጠፍሮ ይይዘዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአተኛን ሰው የገዛ ራሱ ክፋት ያጠምደዋል፤ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአት ሰውን ያጠምዳል፥ ሁሉም በኀጢአቱ ልባብ ይታሰራል። |
ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም!
እነሆ፥ ይህን አላውቀውም ብትል፥ ልቦችን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ነፍስህንም የሚመለከት እርሱ አያውቅምን? ለሰውስ ሁሉ እንደ ሥራው አይመልስለትምን?
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረ ነገር መርምሬ አገኘሁ፤ እርሷም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ ሴት ናት፥ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
ክፋትሽ ይቀጣሻል ክህደትሽ ይገሥጽሻል፤ ጌታን አምላክሽን መተውሽ ምን ያኽል ክፉና መራራ ነገር እንደሆነ እወቂም፥ ተመልከቺም፤ እኔን መፍራት በአንቺ ውስጥ የለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ኖን። የኃጢአቶቼ ቀንበር በእጁ ተይዛለች፥ ታስረው በአንገቴ ላይ ወጥተዋል፥ ጉልበቴን አደከመ። ጌታ በፊታቸው እቆም ዘንድ በማልችላቸው እጅ አሳልፎ ሰጠኝ።