በክፉዎች መንገድ አትግባ፥ በመጥፎ ሰዎችም ጎዳና አትሂድ።
ወደ ኃጥኣን ጐዳና እግርህን አታንሣ፤ በክፉ ሰዎች መንገድ አትሂድ፤
ክፉ ሰዎች በሚሄዱበት መንገድ አትሂድ፤ ምሳሌነታቸውንም አትከተል።
በክፉዎች መንገድ አትሂድ፥ በክፉ ሰዎችም ጎዳና አትቅና።
ብፁዕ ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በፌዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።
ልጄ ሆይ፥ ኃጢአተኞች ቢያባብሉህ እሺ አትበል።
ልጄ ሆይ፥ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፥ ከጎዳናቸውም እግርህን አርቅ፥
ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፥ የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።
መንገዱን ተምረህ፥ ለነፍስህም ወጥመድ እንዳታገኝህ።
በክፉ ሰዎች አትቅና፥ ከእነርሱ ጋርም መሆንን አትመኝ፥
ከእርሷ ራቅ፥ አትሂድባትም፥ ራቅ በል ተዋትም።
መንገድህን ከእርሷ አርቅ፥ ወደ ቤትዋም ደጅ አትቅረብ፥
በአደባባይ ሲሄድ በቤትዋም አቅራቢያ ሲያልፍ፥ የቤትዋን መንገድ ይዞ ወደ እርሷ አቀና፥
አላዋቂነትን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በማስተዋልም መንገድ ሂዱ።”
አትሳቱ፤ “መጥፎ ጓደኝነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።”