ምሳሌ 4:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተግሣጽን ያዝ፥ አትተውም፥ ጠብቀው፥ እርሱ ሕይወትህ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክርን አጥብቀህ ያዛት፤ አትልቀቃት፤ ጠብቃት፤ ሕይወትህ ናትና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተማርከው ትምህርት ሕይወትን ስለሚሰጥህ አጥብቀህ ያዘው፤ አትተወው፤ ደኅና አድርገህም ጠብቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምክሬን ያዝ፥ አትተውም፤ ለራስህ ጠብቃት፥ እርሷ ሕይወትህ ናትና። |
ከእነርሱም ጥቂት እልፍ ብዬ ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት፥ ያዝሁትም ወደ እናቴም ቤት ወደ ወለደችኝም እልፍኝ እስካገባው ድረስ አልተውሁትም።
ይህ ነገር ለእናንተ ሕይወታችሁ ነው እንጂ ከንቱ ነገር አይደለም። በዚህም ነገር ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ለመውረስ በምትገቡባት ምድር ረጅም ዘመን ትኖራላችሁ።”
“የት እንደምትኖር አውቃለሁ፥ የሰይጣን ዙፋን ባለበት ነው፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ በእኔ ያለህን እምነት አልካድህም።