Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማሕልየ መሓልይ 3:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከእነርሱም ጥቂት እልፍ ብዬ ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት፥ ያዝሁትም ወደ እናቴም ቤት ወደ ወለደችኝም እልፍኝ እስካገባው ድረስ አልተውሁትም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከእነርሱ ጥቂት ዕልፍ እንዳልሁ፣ ውዴን አገኘሁት፤ ያዝሁት፤ ወደ እናቴ ቤት እስካመጣው፣ በማሕፀን ወደ ተሸከመችኝም ዕልፍኝ እስካገባው ድረስ አልለቀውም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከእነርሱም ጥቂት አለፍ እንዳልኩ ልቤ የምትወደውን አገኘሁት፤ እንዳያመልጠኝም አጥብቄ ያዝኩት፤ ወደ እናቴም ቤት ወሰድኩት፤ እኔ ወደተወለድኩበትም ክፍል አስገባሁት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከእ​ነ​ር​ሱም ጥቂት እልፍ ብዬ ያን​ጊዜ ነፍሴ የወ​ደ​ደ​ች​ውን አገ​ኘ​ሁት፥ ያዝ​ሁ​ትም፤ ወደ እና​ቴም ቤት፥ ወደ ወላጅ እና​ቴም እል​ፍኝ እስ​ካ​ገ​ባው ድረስ አል​ተ​ው​ሁ​ትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከእነርሱም ጥቂት እልፍ ብዬ ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት፥ ያዝሁትም ወደ እናቴም ቤት ወደ ወላጅ እናቴም እልፍኝ እስካገባው ድረስ አልተውሁትም።

Ver Capítulo Copiar




ማሕልየ መሓልይ 3:4
21 Referencias Cruzadas  

መርቼ ወደ እናቴ ቤት ባገባሁህ፥ በዚያም አንተ ባስተማርከኝ፥ እኔም ከመልካሙ ወይን ጠጅ ከሮማኔም ውኃ ባጠጣሁህ ነበር።


እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥ ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል።


ተግሣጽን ያዝ፥ አትተውም፥ ጠብቀው፥ እርሱ ሕይወትህ ነውና።


“ጠይቁ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል።


ጤት። ጌታ በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው።


እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።


በስውር ወይም በጨለማ ምድር አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፦ በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም፤ እኔ ጌታ እውነትን እናገራለሁ ትክክለኛውንም አወራለሁ።


ሳላውቅ ነፍሴ በከበረው ሠረገላ ላይ አስቀመጠችኝ።


ከላይ የሆነችው ኢየሩሳሌም ግን ነጻ ናት፤ እርሷም እናታችን ናት።


እነሆ ኢየሱስ አገኛቸውና “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት።


ራስሽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ በላይሽ ነው፥ የራስሽም ጠጉር እንደ ሐምራዊ ሐር ነው፥ ንጉሡ በሹርባው ታስሮአል።


ከዚያ ሰውየው፦ “የንጋት ጎህ ሊቀድ ነውና ልቀቀኝ” አለው። እርሱም፦ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው።


ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? መከራ ወይስ ሥቃይ፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ረሃብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ አደጋ፥ ወይስ ሰይፍ?


ከፍታም ቢሆን፥ ጥልቀትም ቢሆን፥ ሌላ ፍጥረትም ቢሆን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።


ነፍሴ የወደደችህ አንተ ንገረኝ፥ ወዴት ታሰማራለህ? በቀትርስ ጊዜ ወዴት ትመስጋለህ? ስለ ምንስ ከባልንጀሮችህ መንጎች በኋላ እቅበዘበዛለሁ?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios