ምሳሌ 27:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሃብት ለዘለዓለም አይኖርምና፥ ዘውድም ለትውልድ ሁሉ አይጸናምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሀብት ለዘላለም አይኖርምና፤ ዘውድም ከትውልድ ወደ ትውልድ ጸንቶ አይኖርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብት ለዘወትር የሚኖር አይደለም፤ መንግሥታትም ቢሆኑ ዘለዓለም አይኖሩም። |
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መጠምጠሚያውን አውልቅ፥ ዘውዱንም አርቅ፤ ይህ እንዲህ አይሆንም፤ የተዋረደውን ከፍ አድርግ፥ ከፍ ያለውንም አዋርድ።
በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፥ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ አስፈሪ ፍፃሜ ያመጣባቸዋልና።
አሁን ግን መንግሥትህ አይጸናም፤ ጌታ እንደ ልቡ የሚሆንለትን ሰው አግኝቶአል፤ አንተ የጌታን ትእዛዝ ባለመጠበቅህም፥ እርሱን የሕዝቡ መሪ አድርጎ መርጦታል።”