አባቶችህ የሠሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፋልስ።
የቀድሞ አባቶችህ ያስቀመጡትን፣ የጥንቱን የወሰን ምልክት አታፋልስ።
የቀድሞ አባቶችህ ያኖሩትን የወሰን ምልክት አትለውጥ።
አባቶችህ የሠሩትን የቀድሞውን ድንበር አታፍርስ።
የድንበሩን ምልክት የሚያፈርሱ አሉ፥ መንጋዎቹን ቀምተው ያሰማራሉ።
የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍልስ፥ ወደ ድሀ አደጎች እርሻ አትግባ፥
እንደ ክፉ ሰው በጻድቅ ቤት ላይ አትሸምቅ፥ ማደሪያውንም አታውክ።
“አምላክህ ጌታ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ለአንተ በሚተላለፍልህ ርስት ላይ የቀድሞ ሰዎች ያስቀመጡትን የባልጀራህን የድንበር ምልክት አታንሣ።
“‘የባልንጀራውን የድንበር ምልክት ከቦታው የሚያንቀሳቅስ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።