የምር ቃል እንደሚገቡ፥ ለባለ ዕዳዎች እንደሚዋሱ አትሁን፥
በዋስትና ቃል እጅ አትምታ፤ ለብድር ተያዥ አትሁን፤
የሌላ ሰው ዕዳ ለመክፈል ዋስ አትሁን፤
የሰውን ፊት በማፈር ራስህን ለዋስትና አትስጥ።
ለእንግዳ ሰው የሚዋስ ክፉ መከራን ይቀበላል፥ ዋስ መሆንን የሚጠላ ግን ይድናል።
አእምሮ የጐደለው ሰው አጋና ይመታል፥ በባልንጀራውም ፊት ይዋሳል።
ለማያውቀው ከተዋሰ ሰው ልብሱን ውሰድ፥ ለእንግዳ ሰው የተዋሰውንም ለመያዣነት አስቀረው።