ምሳሌ 21:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኩሩና ተጓዳጅ ሰው ፌዘኛ ይባላል፥ እርሱም በትዕቢት ቁጣ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትዕቢተኛና ኵሩ ሰው “ፌዘኛ” ይባላል፤ በጠባዩም እብሪተኛ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕቢተኛና ትምክሕተኛ ሰው ፌዘኛ ነው፤ ድርጊቱም በትዕቢት የተሞላ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የችኩል፥ የነዝናዛና የነገረኛ ሰው ስሙ ቸነፈር ነው፥ ክፉን የሚያስብም ኃጥእ ነው። |
በእርግጥ ወይን አታላይ ነው፤ ትዕቢተኛ ሰው በስፍራው አርፎ አይቀመጥም፤ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፤ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል።
ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ እንዳታለሉት በተረዳ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፥ ወታደሮችን ልኮ ከሰብአ ሰገል በተረዳው ዘመን መሠረት፥ ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን በቤተ ልሔምና በአካባቢዋ የነበሩትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።