La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 17:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዓመፃን የሚወድድ ክርክርን ይወድዳል፥ ደጁንም ዘለግ የሚያደርግ ውድቀትን ይሻል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጠብ የሚወድድ ኀጢአትን ይወድዳል፤ በሩን ከፍ አድርጎ የሚሠራም ጥፋትን ይጋብዛል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኃጢአትን የሚወድ ጠብን ይወዳል፤ ከፍ ብሎ እንደ ተሠራ ደጃፍ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሰው ውድቀትን ይጋብዛል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ክርክርን የሚወድድ በጠብ ደስ ይለዋል።

Ver Capítulo



ምሳሌ 17:19
14 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ሠረገላና ፈረሶች፥ ፊት ፊቱም የሚሮጡ አምሳ ሰዎች አዘጋጀ።


ያንጊዜ የሐጊት ልጅ አዶንያስ፦ “ንጉሥ እሆናለሁ” ብሎ ተነሣሣ፤ ለራሱም ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን፥ እንዲሁም ኀምሳ ጋሻ ጃግሬዎችን አዘጋጀ።


ትዕቢት ጥፋትን፥ ኩሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።


የጠብ መጀመሪያ እንደ ውኃ አፈሳሰስ ነው፥ ስለዚህ ጠብ ሳይበረታ አንተ ክርክርን ተው።


ሰው ሳይወድቅ በፊት ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።


ሥራህን በውጭ አሰናዳ፥ ለራስህ በእርሻ ውስጥ አዘጋጀው፥ ከዚያም በኋላ ቤትህን ሥራ።


ጠቢብ ከሞኝ ጋር ቢጣላ፥ ሞኙ ወይም ይቈጣል ወይም ይስቃል፥ ዕረፍትም አይኖርም።


ወደ እናንት ስመጣ፥ እኔ እንደምፈልገው ሆናችሁ ላላገኛችሁ እችላለሁ ወይም እናንተ እንደምትፈልጉኝ ሆኜ ላታገኙኝ ትችላላችሁ ብዬ እፈራለሁ፤ ምናልባት ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኝነት፥ ሐሜት፥ ማሾክሾክ፥ ኩራት፥ ሁከትም ይኖር ይሆን ብዬ እሰጋለሁ።


የሰው ቁጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና።