በዚያን ጊዜም ዳዊት እንዲህ አለ፦ “የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙ፥ ለዘለዓለሙም እንዲያገለግሉት ጌታ ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር ማንም የጌታን ታቦት ሊሸከም አይገባውም።”
ዘኍል 3:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሌዊን ነገድ አምጥተህ አቅርብ እንዲያገለግሉትም በካህኑ በአሮን ፊት አቁማቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሌዊን ነገድ አምጥተህ ካህኑን አሮንን በአገልግሎቱ እንዲረዱት ከፊቱ አቁማቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሌዊን ነገድ አቅርበህ ለካህኑ አሮን አገልጋዮች እንዲሆኑ መድባቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሌዊን ነገድ አቅርበህ ያገለግሉት ዘንድ በካህኑ በአሮን ፊት አቁማቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሌዊን ነገድ አቅርበህ ያገለግሉት ዘንድ በካህኑ በአሮን ፊት አቁማቸው። |
በዚያን ጊዜም ዳዊት እንዲህ አለ፦ “የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙ፥ ለዘለዓለሙም እንዲያገለግሉት ጌታ ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር ማንም የጌታን ታቦት ሊሸከም አይገባውም።”
“ሥራቸውም የጌታን ቤት በየአደባባዩና በየጓዳው ውስጥ በሚሰጡተት አገልግሎት አሮንን ልጆች መርዳት፥ ቅዱሱንም ዕቃ ሁሉ ማንጻት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት አገልግሎት መሥራት ነበረ።
ለጌታም ቤት አገልግሎት የመገናኛውን ድንኳን ሥርዓት የመቅደሱንም ሥርዓት የወንድሞቻቸውንም የአሮንን ልጆች ሥርዓት በመጠበቅ ያገለግሉ ነበረ።”
በሙሴም መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት በኢየሩሳሌም ባለው በእግዚአብሔር አገልግሎት ላይ ካህናቱን በየማዕረጋቸው ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው መደቡአቸው።
“ከዚያም በኋላ በሰፈሮቹም መካከል የመገናኛው ድንኳን ከሌዋውያን ሰፈር ጋር ይጓዛል፤ እንደ ሰፈራቸው እያንዳንዱ ሰው ስፍራቸውን ይዘው በየዓላሞቻቸው ይጓዛሉ።
በዚያን ጊዜ የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከም፥ እርሱንም ለማገልገል በጌታ ፊት እንዲቆም፥ በስሙም እንዲባርክ ጌታ እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ።