ዘኍል 29:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለወይፈኖቹና ለአውራ በጎቹ ለጠቦቶቹም የእህል ቁርባናቸውንና የመጠጥ ቁርባናቸውን እንደ ቁጥራቸው መጠን እንደ ሕጉ ታቀርባላችሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋራ በተወሰነው ቍጥር መሠረት የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን ዐብራችሁ አቅርቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእህሉንና የመጠጡን ቊርባን ከኰርማዎቹ፥ ከአውራ በጎቹ፥ ከጠቦቶቹ መሥዋዕት ጋር ለየብዛታቸው በተወሰነው መሠረት ታቀርባላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለበሬዎቹና ለአውራ በጎቹ፥ ለጠቦቶቹም የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን እንደ ቍጥራችው መጠን እንደ ሕጉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለወይፈኖቹና ለአውራ በጎቹ ለጠቦቶቹም የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቁርባናቸውን እንደ ቍጥራቸው መጠን እንደ ሕጉ፥ |
ከእንጀራውም ጋር ነውር የሌለባቸውን የአንድ ዓመት ሰባት ተባት ጠቦቶች፥ አንድ ወይፈንም፥ ሁለትም አውራ በጎች ታቀርባላችሁ። ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ሆኖ ከእህል ቁርባናቸውና ከመጠጥ ቁርባናቸው ጋር ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናሉ።
የመጠጥ ቁርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሢሶ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል፤ ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።
በወሩ መባቻ ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን፥ ዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን፥ ከመጠጡም ቁርባን ሌላ፥ እንደ ሕጋቸው ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርቡ ናቸው።