Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 29:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋራ በተወሰነው ቍጥር መሠረት የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን ዐብራችሁ አቅርቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ለወይፈኖቹና ለአውራ በጎቹ ለጠቦቶቹም የእህል ቁርባናቸውንና የመጠጥ ቁርባናቸውን እንደ ቁጥራቸው መጠን እንደ ሕጉ ታቀርባላችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የእህሉንና የመጠጡን ቊርባን ከኰርማዎቹ፥ ከአውራ በጎቹ፥ ከጠቦቶቹ መሥዋዕት ጋር ለየብዛታቸው በተወሰነው መሠረት ታቀርባላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ለበ​ሬ​ዎ​ቹና ለአ​ውራ በጎቹ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን እንደ ቍጥ​ራ​ችው መጠን እንደ ሕጉ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ለወይፈኖቹና ለአውራ በጎቹ ለጠቦቶቹም የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቁርባናቸውን እንደ ቍጥራቸው መጠን እንደ ሕጉ፥

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 29:18
8 Referencias Cruzadas  

“ ‘ማንኛውም ሰው የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ዱቄቱ የላመ ይሁን፤ ዘይት ያፍስስበት፤ ዕጣንም ይጨምርበት፤


ከእንጀራውም ጋራ ሰባት ነውር የሌለባቸው የአንድ ዓመት እንከን የሌለው ተባዕት የበግ ጠቦቶች፣ አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች አቅርቡ፤ እነዚህም ከእህል ቍርባናቸውና ከመጠጥ ቍርባናቸው ጋራ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናሉ፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ነው።


ከእያንዳንዱ ወይፈን ጋራ ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን የሂን ግማሽ የወይን ጠጅ፣ ከአውራው በግ ጋራ የሂን አንድ ሦስተኛ፣ ከእያንዳንዱም የበግ ጠቦት ጋራ የኢን አንድ አራተኛ የወይን ጠጅ ይቅረብ፤ ይህም በየወሩ መባቻ ዓመቱን ሙሉ የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።


ከእያንዳንዱ ጠቦት ጋራ ዐብሮት የሚቀርበውም የመጠጥ ቍርባን ፈልቶ የወጣለት የሂን አንድ አራተኛ መጠጥ ይሆናል፤ የመጠጡንም ቍርባን በተቀደሰው ቦታ ላይ ለእግዚአብሔር አፍስሱት።


እነዚህ እንግዲህ በተደነገገው መሠረት ከእህል ቍርባናቸውና ከመጠጥ ቍርባናቸው ጋራ በየዕለቱና በየወሩ ከሚቀርቡት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሌላ ተጨማሪ ሆነው፣ ለእግዚአብሔር ሽታቸው ደስ የሚያሰኝ በእሳት የሚቀርቡ መሥዋዕቶች ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos