ዘኍል 24:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኪቲም ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፥ አሦርንም ያሠቃያሉ፥ ዔቦርንም ያስጨንቃሉ፤ እርሱም ደግሞ ወደ ጥፋት የሚያመራ ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም መርከቦች ከኪቲም ዳርቻዎች ይመጣሉ፤ አሦርንና ዔቦርን ይይዛሉ፤ እነርሱም ደግሞ ይደመሰሳሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወራሪዎች በመርከብ ከቆጵሮስ ይመጣሉ፤ እነርሱም አሦርንና ዔቤርን ያጠፋሉ፤ እነርሱም ራሳቸው ለዘለዓለም ይጠፋሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቄጤዎንም እጅ የሚወጣው አሦርንና ዕብራውያንን ያስጨንቃል፤ እነርሱም በአንድነት ይጠፋሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኪቲም ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፥ አሦርንም ያስጨንቃሉ፥ ዔቦርንም ያስጨንቃሉ፤ እርሱም ደግሞ ወደ ጥፋት ይመጣል። |
አንድ የሸሸ ሰውም መጣ፥ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው፥ እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊ መምሬ የባሉጥ ዛፎች አጠገብ ይኖር ነበር፥ እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር።
ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፤ እንዲህ ይላል የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤
በለዓምም አማሌቅን አይቶ ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “የአሕዛብ መጀመሪያ የሆነ አማሌቅ ነበረ፤ ፍጻሜው ግን ወደ ጥፋት የሚያመራ ይሆናል።”