ዘኍል 21:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀስትን ወረወርንባቸው፤ ከሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፉ፤ እሳቱ እስከ ሜድባ እስኪዛመት ድረስ ደመሰስናቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኛ ግን ገለበጥናቸው፤ ሐሴቦን እስከ ዲቦን ድረስ ተደመሰሰች፤ እስከ ኖፋ ድረስ ያሉትን፣ እስከ ሜድባ የተዘረጉትን እንዳሉ አፈራርሰናቸዋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ዘሮቻቸው ተደመሰሱ ከሐሴቦን እስከ ዲቦን፥ እሳቱ እስከ ሜዴባ እስኪስፋፋ ድረስ አጠፋናቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘራቸውም ከሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፋ፤ ሴቶቻቸውም ደግሞ በሞዓብ ላይ እሳትን አነደዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገተርናቸው፤ ከሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፉ፤ ኖፋም እስኪደርሱ እስከ ሜድባ አፈረስናቸው። |
ከዚያም ባለፍላጻዎቹ ከግንቡ ላይ ሆነው በእኛ በአገልጋዮችህ ላይ ቀስት ስለ ለቀቁ፥ ከንጉሡ አገልጋዮች ጥቂቶቹን ገደሉ፤ አገልጋይህ ሒታዊው ኦርዮም ሞተ።”
ሠላሳ ሁለትም ሺህ ሰረገሎች የመዓካንም ንጉሥ ሠራዊት ቀጠሩ፤ መጥተውም በሜድባ ፊት ለፊት ሰፈሩ። የአሞንም ልጆች ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ወደ ውግያ መጡ።
ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፤ ሞዓብ በናባውና በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፤ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቷል።
የዲሞንም ውኃ ደም ተሞልታለች፤ ገና በዲሞን ላይ ሥቃይን እጨምራለሁ፥ ከሞዓባውያንም በሚያመልጡ፥ ከምድርም በሚቀሩ ላይ አንበሳን እሰዳለሁ።