Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 21:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ስለዚህ ዘሮቻቸው ተደመሰሱ ከሐሴቦን እስከ ዲቦን፥ እሳቱ እስከ ሜዴባ እስኪስፋፋ ድረስ አጠፋናቸው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 “እኛ ግን ገለበጥናቸው፤ ሐሴቦን እስከ ዲቦን ድረስ ተደመሰሰች፤ እስከ ኖፋ ድረስ ያሉትን፣ እስከ ሜድባ የተዘረጉትን እንዳሉ አፈራርሰናቸዋል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ቀስትን ወረወርንባቸው፤ ከሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፉ፤ እሳቱ እስከ ሜድባ እስኪዛመት ድረስ ደመሰስናቸው።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ዘራ​ቸ​ውም ከሐ​ሴ​ቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፋ፤ ሴቶ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሞ​ዓብ ላይ እሳ​ትን አነ​ደዱ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ገተርናቸው፤ ከሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፉ፤ ኖፋም እስኪደርሱ እስከ ሜድባ አፈረስናቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 21:30
13 Referencias Cruzadas  

ቀስተኞቹ በብርቱ ያጠቁታል፤ በቀስታቸውም እየነደፉ ያሳድዱታል።


ከዚያም በኋላ በግንብ ላይ ሆነው ፍላጻዎችን ወረወሩብን፤ ንጉሥ ሆይ! ከጦር መኰንኖችህ ጥቂቶቹ በዚያን ጊዜ ሞቱ፤ አገልጋይህ ኦርዮም ተገደለ።”


የተከራዩአቸው ሠላሳ ሁለት ሺህ ሠረገሎችና የንጉሥ ማዕካ ሠራዊት መጥተው በሜዳባ አጠገብ ሰፈሩ፤ ዐሞናውያንም ከየከተሞቻቸው ወጥተው ለጦርነት ተዘጋጁ።


ፍላጻውን ከቀስቱ አስፈነጠረ፤ ጠላቶቹንም በተናቸው፤ በመብረቁም ብልጭታ አሳደዳቸው።


የጺቦን ሕዝብም በቤተ ጣዖታቸው ለማልቀስ ወደ ኰረብታ ይወጣሉ፤ የሞአብ ሕዝብ ስለ ነቦና ስለ ሜዳባ ከተሞቻቸው በከባድ ሐዘን ያለቅሳሉ፤ ከሐዘናቸውም የተነሣ ጠጒራቸውንና ጢማቸውን ተላጭተዋል።


በዲቦን ከተማ የሚገኘው ወንዝ በደም የተሞላ ነው፤ ሆኖም በዲቦን ላይ እግዚአብሔር ከዚያ የባሰ ነገር ያመጣል፤ ከሞአብ ሸሽተው የሚያመልጡትንና እዚያም ከሞት የተረፉትን ሁሉ አንበሳ ልኮ ያጠፋቸዋል።


ምሽጎችዋም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ የሚያደርግ ሞአብን የሚደመስሳት እነሆ እዚህ ስለ አለ፥ በዲቦን ከተማ የምትኖሩ ሁሉ ከክብር ቦታችሁ ወርዳችሁ በምድር ትቢያ ላይ ተቀመጡ፤


ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በአሞራውያን ግዛት ውስጥ ተቀመጡ፤


“ይህ እስራኤላውያን እንዲወርሱት እግዚአብሔር የረዳቸው የዐጣሮት፥ የዲቦን፥ የያዕዜር፥ የኒምራ፥ የሐሴቦን፥ የኤልዓሌ፥ የሲብማ፥ የነቦና የበዖን ከተሞች የሚገኙበት ምድር ለከብት ተስማሚ ነው፥ እኛ ደግሞ ብዙ ከብት አለን፤”


የጋድ ነገድ የተመሸጉትን የዲቦንን፥ የዐጣሮትን፥ የዓሮዔርን፥


እንዲሁም ሐሴቦንን፥ በደጋማ አገር ያሉትን ከተሞች፥ ዲቦን፥ ባሞትበዓል፥ ቤትበዓልመዖን፥


ግዛታቸውም ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ከሆነው ከዓሮዔር ተነሥቶ እንዲሁም በሸለቆው መካከል ካለው ከተማ ከሜዴባ ሜዳ እስከ ዲቦን ድረስ ይደርሳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos