La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 19:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን በውኃ ያነጻል፥ በዚህም ንጹሕ ይሆናል፤ ነገር ግን በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ባያነጻ ንጹሕ አይሆንም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሦስተኛውና በሰባተኛውም ቀን ሁለመናውን በውሃው ያንጻ፤ ንጹሕም ይሆናል። በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ካላነጻ ግን ንጹሕ አይሆንም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ለማንጻት በተመደበው ውሃ ራሱን ያነጻል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል፤ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሱን የማያነጻ ከሆነ ሊነጻ አይችልም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ደ​ዚሁ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ሁለ​መ​ና​ውን ያነ​ጻል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል፤ ነገር ግን በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ሁለ​መ​ና​ውን ባያ​ነጻ ንጹሕ አይ​ሆ​ንም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚህም ውኃ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ያጠራል፥ ንጹሕም ይሆናል፤ ነገር ግን በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ባያጠራ ንጹሕ አይሆንም።

Ver Capítulo



ዘኍል 19:12
12 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ በዓመፃ ተወለድሁ፥ እናቴም በኃጢአት ፀነሰችኝ።


በሦስተኛውም ቀን ይዘጋጁ፤ በሦስተኛው ቀን ሕዝቡ ሁሉ እያዩ ጌታ በሲና ተራራ ላይ ይወርዳልና።


ሕዝቡንም፦ “ለሦስተኛው ቀን ተዘጋጁ፥ ወደ ሴትም አትቅረቡ” አላቸው።


በእናንተ ላይ ንጹሕ ውኃ እረጫለሁ እናንተም ትነጻላችሁ፥ ከርኩሰቶቻችሁ ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።


ከሁለት ቀን በኋላ ነፍስ ይዘራብናል፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፥ በፊቱም በሕይወት ያኖረናል።


ከለምጽ ደዌ በሚነጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፤ ከዚያም ንጹሕ ነህ ይለዋል፥ በሕይወትም ያለውን ወፍ በተንጣለለው ሜዳ ላይ እንዲበር ይለቀዋል።


ነገር ግን በሦስተኛው ቀን ከመሥዋዕቱ የተረፈው ሥጋ በእሳት ይቃጠል።


ከሰፈሩም ውጭ ሰባት ቀን ስፈሩ፤ ከእናንተም ሰውን የገደለ ሁሉ የተገደለውንም የነካ ሁሉ፥ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሳችሁንና እናንተ የማረካችኋቸውን አንጹ።


ልባቸውንም በእምነት ሲያነጻ በእኛና በእነርሱ መካከል አንዳች አልለየም።


እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። እንዲህም አለኝም፦ “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሶቻቸውንም አጥበው በበጉ ደም አንጽተዋል።