Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 19:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እን​ደ​ዚሁ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ሁለ​መ​ና​ውን ያነ​ጻል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል፤ ነገር ግን በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ሁለ​መ​ና​ውን ባያ​ነጻ ንጹሕ አይ​ሆ​ንም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በሦስተኛውና በሰባተኛውም ቀን ሁለመናውን በውሃው ያንጻ፤ ንጹሕም ይሆናል። በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ካላነጻ ግን ንጹሕ አይሆንም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን በውኃ ያነጻል፥ በዚህም ንጹሕ ይሆናል፤ ነገር ግን በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ባያነጻ ንጹሕ አይሆንም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ለማንጻት በተመደበው ውሃ ራሱን ያነጻል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል፤ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሱን የማያነጻ ከሆነ ሊነጻ አይችልም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በዚህም ውኃ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ያጠራል፥ ንጹሕም ይሆናል፤ ነገር ግን በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ባያጠራ ንጹሕ አይሆንም።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 19:12
12 Referencias Cruzadas  

እና​ን​ተም ከሰ​ፈሩ ውጭ ሰባት ቀን ስፈሩ፤ ሰውን የገ​ደለ ሁሉ፥ የተ​ገ​ደ​ለ​ው​ንም የዳ​ሰሰ ሁሉ፥ እና​ን​ተና የማ​ረ​ካ​ች​ኋ​ቸ​ውም በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ንጹሕ አድ​ርጉ።


እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። አለኝም “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።


ልባ​ቸ​ው​ንም በእ​ም​ነት አን​ጽቶ ከእኛ አል​ለ​ያ​ቸ​ውም።


ከሁ​ለት ቀን በኋላ ያድ​ነ​ናል፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ያስ​ነ​ሣ​ናል፤ በፊ​ቱም በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን።


ጥሩ ውኃ​ንም እረ​ጭ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ከር​ኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ አነ​ጻ​ች​ኋ​ለሁ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረዳቱ ያላ​ደ​ረገ፥ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ቱም ብዛት የታ​መነ፥ በከ​ንቱ ነገ​ርም የበ​ረታ ያ ሰው እነሆ።”


ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም ሥጋ እስከ ሦስ​ተ​ኛው ቀን የሚ​ቈ​የ​ውን በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል።


ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ለሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተዘ​ጋጁ፤ ወደ ሴቶ​ቻ​ች​ሁም አት​ቅ​ረቡ” አለ።


በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ተራራ ላይ ይወ​ር​ዳ​ልና ለሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተዘ​ጋ​ጅ​ተው ይጠ​ብቁ።


ከለ​ም​ጹም በሚ​ነ​ጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረ​ጫል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል፤ ያል​ታ​ረ​ደ​ች​ውን ዶሮ ወደ ሜዳ ይለ​ቅ​ቃ​ታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios