ዘኍል 16:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ “እናንተ የጌታን ሕዝብ ገድላችኋል” ብለው በሙሴና በአሮን ላይ አጉረመረሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ፣ “እናንተ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ገድላችኋል” በማለት በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ መላው የእስራኤል ማኅበር “የእግዚአብሔር ወገኖች የሆኑትን ሕዝብ ገድላችኋል” በማለት በሙሴና በአሮን ላይ አጒረመረሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋውም የእስራኤል ልጆች ሁሉ፥ “እናንተ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ገድላችኋል” ብለው በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋውም የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ እናንተ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ገድላችኋል ብለው በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ። |
አለቆቹም ንጉሡን፦ “ይህን የመሰለውን ቃላት እየነገራቸው የሕዝቡን ሁሉ እጅ በዚህችም ከተማ የቀሩትን የወታደሮቹን እጅ እያደከመ ነውና ይህ ሰው እንዲገደል እንለምንሃለን፤ ይህ ሰው ክፋትን እንጂ ለዚህ ሕዝብ ሰላምን አይመኝለትምና” አሉት።
ነገር ግን ከለዳውያን እንዲገድሉን ወደ ባቢሎንም ማርከው እንዲወስዱን በእጃቸው አሳልፈህ ልትሰጠን የኔርያ ልጅ ባሮክ በላያችን ላይ አነሣሥቶሃል።”
የቤቴልም ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም እንዲህ ብሎ ላከ፦ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል አሢሮብሃል፤ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጉረመረሙ፤ ማኅበሩም ሁሉ እንዲህ አሉአቸው፦ “በግብጽ ምድር ሳለን ምነው በሞትን ኖሮ! ወይም በዚህ ምድረ በዳ ምነው በሞትን ኖሮ!
ሊቀ ካህናቱም “በዚህ ስም እንዳታስተምሩ አጥብቀን አላዘዝናችሁምን? እነሆም፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋል፤ የዚያንም ሰው ደም በእኛ ታመጡብን ዘንድ ታስባላችሁ፤” ብሎ ጠየቃቸው።