ነህምያ 4:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ደግሞ በዚያ ጊዜ ሕዝቡን፦ “በሌሊት ጠባቂዎች፥ በቀንም ሥራ እንዲሰሩልን እያንዳንዱ ከአገልጋዩ ጋር በኢየሩሳሌም ውስጥ ይደር፤” አልኋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ ቀን ጀምሮ ከሰዎቼ እኩሌቶቹ ሥራውን ሠሩ፤ የቀሩት ደግሞ ጋሻና ጦር፣ ቀስትና ጥሩር ይዘው ነበር። የጦር አለቆች ከመላው የይሁዳ ሕዝብ በስተኋላ ቆሙ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም ጊዜ ጀምሮ እኔ ያሰለፍኳቸው ሰዎች እኩሌቶቹ ሲሠሩ፥ እኩሌቶቹ ጥሩር ለብሰው፥ ጦር ይዘው፥ ጋሻ አንግበው፥ ቀስት ደግነው ዘብ በመቆም እንዲጠብቁ አደረግሁ፤ መሪዎቻችንም ለሕዝቡ ሙሉ ድጋፍ ይሰጡ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ቀን ጀምሮ እኩሌቶቹ ብላቴኖች ሥራ ይሠሩ ነበር፤ እኩሌቶቹም ጋሻና ጦር፥ ቀስትና ጥሩርም ይዘው በፊትና በኋላ ይጠብቁ ነበር፤ አለቆቹም ከይሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ቀን ጀምሮ እኩሌቶቹ ብላቴኖቼ ሥራ ይሠሩ ነበር፥ እኩሌቶቹም ጋሻና ጦር ቀስትና ጥሩርም ይዘው ነበር፥ አለቆቹም ከይሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር። |
እኔ፥ ወንድሞቼ፥ ጎበዛዝቶቼና ከኋላዬ የነበሩት ጠባቂዎች ልብሳችንን አናወልቅም ነበር። ወደ ውኃም ስንሄድ እያንዳንዱ መሣሪያውን ይዞ ይሄድ ነበር።